Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អើររ៉ក់ទ៍   អាយ៉ាត់:
لَهُۥ دَعۡوَةُ ٱلۡحَقِّۚ وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسۡتَجِيبُونَ لَهُم بِشَيۡءٍ إِلَّا كَبَٰسِطِ كَفَّيۡهِ إِلَى ٱلۡمَآءِ لِيَبۡلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَٰلِغِهِۦۚ وَمَا دُعَآءُ ٱلۡكَٰفِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ
14. ለእርሱ(አላህ) የእውነት ጥሪ አለው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው ጣዖታት ምሳሌው ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን በሩቅ ሆኖ እንደሚዘረጋና እንደማይደርስባት ሰው እንጂ ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸዉም:: እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም:: የከሓዲያን ጥሪ በከንቱ ልፋት እንጂ ሌላ አይደለም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِلَّهِۤ يَسۡجُدُۤ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ طَوۡعٗا وَكَرۡهٗا وَظِلَٰلُهُم بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡأٓصَالِ۩
15. በሰማያትና በምድር ያሉት ሁሉ በዉድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ:: ጥላዎቻቸዉም በጧቶችና በማታዎች ይሰግዳሉ:: (1)
(1) እዚህ አንድ ሱጁድ ይደረጋል። የቁርኣን ንባብ ሱጁድ (ሱጁዱትላዋህ) ይባላል። በቁርኣን ውስጥ 15 ቦታዎች ይገኛል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ قُلِ ٱللَّهُۚ قُلۡ أَفَٱتَّخَذۡتُم مِّن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ لَا يَمۡلِكُونَ لِأَنفُسِهِمۡ نَفۡعٗا وَلَا ضَرّٗاۚ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُ أَمۡ هَلۡ تَسۡتَوِي ٱلظُّلُمَٰتُ وَٱلنُّورُۗ أَمۡ جَعَلُواْ لِلَّهِ شُرَكَآءَ خَلَقُواْ كَخَلۡقِهِۦ فَتَشَٰبَهَ ٱلۡخَلۡقُ عَلَيۡهِمۡۚ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّٰرُ
16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?» በላቸው:: «አላህ ነው።» በልም። «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትን የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደ እርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አረጉለትና ፍጥረቱ በእነርሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» በልም። «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው:: እርሱም ብቸኛውና ሁሉን አሸናፊው ነው።» በል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَسَالَتۡ أَوۡدِيَةُۢ بِقَدَرِهَا فَٱحۡتَمَلَ ٱلسَّيۡلُ زَبَدٗا رَّابِيٗاۖ وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيۡهِ فِي ٱلنَّارِ ٱبۡتِغَآءَ حِلۡيَةٍ أَوۡ مَتَٰعٖ زَبَدٞ مِّثۡلُهُۥۚ كَذَٰلِكَ يَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ وَٱلۡبَٰطِلَۚ فَأَمَّا ٱلزَّبَدُ فَيَذۡهَبُ جُفَآءٗۖ وَأَمَّا مَا يَنفَعُ ٱلنَّاسَ فَيَمۡكُثُ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ كَذَٰلِكَ يَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَالَ
17. ከሰማይ ውሃን አወረደ:: ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ:: ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ:: ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል:: የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል:: ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል:: ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِرَبِّهِمُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَٱلَّذِينَ لَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُۥ لَوۡ أَنَّ لَهُم مَّا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفۡتَدَوۡاْ بِهِۦٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ سُوٓءُ ٱلۡحِسَابِ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ
18. ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት ሰዎች መልካም ነገር ገነት አለላቸው:: እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነርሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር:: እነዚያ ለእነርሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ፍራሻቸዉም ገሀነም ከፋች!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អើររ៉ក់ទ៍
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ