Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
وَلَا تَقۡرَبُواْ مَالَ ٱلۡيَتِيمِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ أَشُدَّهُۥۚ وَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۖ وَإِذَا قُلۡتُمۡ فَٱعۡدِلُواْ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰۖ وَبِعَهۡدِ ٱللَّهِ أَوۡفُواْۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
«የየቲምንም ገንዘብ ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪ ደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጅ አትቅረቡ፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም በትክክሉ ሙሉ፡፡ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፡፡ በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ (እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنَّ هَٰذَا صِرَٰطِي مُسۡتَقِيمٗا فَٱتَّبِعُوهُۖ وَلَا تَتَّبِعُواْ ٱلسُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمۡ عَن سَبِيلِهِۦۚ ذَٰلِكُمۡ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ تَمَامًا عَلَى ٱلَّذِيٓ أَحۡسَنَ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لَّعَلَّهُم بِلِقَآءِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ
ከዚያም ለሙሳ በዚያ መልካም በሠራው ላይ (ጸጋችንን) ለማሟላት ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር መጽሐፉን (ለእስራኤል ልጆች) መሪና እዝነት ይኾን ዘንድ ሰጠነው፡፡ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ሊያምኑ ይከጀላልና፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَهَٰذَا كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ مُبَارَكٞ فَٱتَّبِعُوهُ وَٱتَّقُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ
ይህም ያወረድነው የኾነ የተባረከ መጽሐፍ ነው፡፡ ተከተሉትም፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ (ከክህደት) ተጠንቀቁ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَن تَقُولُوٓاْ إِنَّمَآ أُنزِلَ ٱلۡكِتَٰبُ عَلَىٰ طَآئِفَتَيۡنِ مِن قَبۡلِنَا وَإِن كُنَّا عَن دِرَاسَتِهِمۡ لَغَٰفِلِينَ
«(ያወረድነውም) መጽሐፍ የተወረደው ከፊታችን በሁለቱ ጭፍሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ እኛም ከንባባቸው ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوۡ تَقُولُواْ لَوۡ أَنَّآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا ٱلۡكِتَٰبُ لَكُنَّآ أَهۡدَىٰ مِنۡهُمۡۚ فَقَدۡ جَآءَكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞۚ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَصَدَفَ عَنۡهَاۗ سَنَجۡزِي ٱلَّذِينَ يَصۡدِفُونَ عَنۡ ءَايَٰتِنَا سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يَصۡدِفُونَ
ወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነሱ ይበልጥ የተመራን እንኾን ነበር» እንዳትሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፣ መምሪያም፣ እዝነትም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ በአላህም አንቀጾች ካስተባበለና ከእርሷም ከዞረ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያን አንቀጾቻችንን የሚተውትን ይተውት በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

បានបកប្រែដោយលោកម៉ូហាំម៉ាត់ សទុីក និងលោកអាស់សានី ហាប៊ុីប។ ត្រូវបានអភិវឌ្ឍន៍ដោយការត្រួតពិនិត្យពីមជ្ឍមណ្ឌលបកប្រែរ៉ូវ៉ាទ ការបកប្រែដើមអាចចូលមើលបានក្នុងគោលបំណងផ្តល់យោបល់ វាយតម្លៃ និងអភិវឌ្ឍន៍បន្ត។

បិទ